IDEAS home Printed from https://ideas.repec.org/p/zbw/idospb/283123.html
   My bibliography  Save this paper

ለስደተኞች እና ለስደተኛ ተቀባይ ማህበረሰቦች የስራ እድል እና ማህበራዊ ትስስርን ለማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና (Tvet) ያለው ሚና
[Improving employment and social cohesion among refugee and host communities through TVET: evidence from an impact assessment in Ethiopia]

Author

Listed:
  • Getachew, Abis
  • Höckel, Lisa Sofie
  • Kuhnt, Jana
  • Muhumad, Abdirahman A.
  • von Schiller, Armin

Abstract

መንግስታት እና ለጋሾች በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና (ቴሙትስ) አማካኝነት የሥራ ዕድሎችን እና ምርታማነትን የማሳደግ ከፍተኛ ምኞት አላቸው። ሥልጠናው በዋናነት የሥራ ገበያው የሚፈልገውን ሙያ በማስተማር ብቃት ያለው የሰው ኃይል አቅርቦትን ማመቻቸት ይጠበቅበታል። እነዚሁ አካላት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ከሥራ ስምሪት ባሻገር አካታችነትን፣ የፆታ እኩልነትን እና ማኅበራዊ ትስስርን (social cohesion) በኅብረተሰቡ ውስጥ እንደሚያሻሽል ይገምታሉ። የሥራ እድል ተደራሽነት ፤ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን በማጎልበት እንዲሁም ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም ረገድ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል። በስደት ረዥም ጊዜ መቆየት እና ወደሶስተኛ አገር የሚደረጉ የቋሚ መፍትሄ እድሎች ማሽቆልቆል፤ የስደተኞች የመጀመርያ መዳረሻ አገሮች ውስጥ ማኅበራዊ ውህደት (local integration) ፍለጋን አነሳስቷል። ባለፉት አስርት ዓመታት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው ከዚህ አንፃር ነው። የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የእነዚህን መንግስታት እና ለጋሾች ምኞቶች ያሟላ ነው? በአጠቃላይ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ላይ ያሉ ተጨባጭ ማስረጃዎች ውስን እና በአብዛኛው ወጥነት የሌላቸው ናቸው። ከሥራና ከገቢ አንፃር ሲታይ ትንሽ አወንታዊ ውጤት እንዳለ መረጃዎች ቢጠቁሙም በአብዛኛው ውጤቶች የሚታዩት ከመካከለኛ እስከ ረዥም ጊዜ (Medium and long term) ሲሆን፣ በአጠቃላይ ፕሮግራሞቹ ለረጅም ጊዜ ሥራ አጦች በተሻለ ሁኔታ ይሰራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና በማኅበራዊ ትስስር ዙሪያ ሊያመጣ የሚችለውን ውጤት በተመለከተ ትልቅ የእውቀት ክፍተት አለ። በፖሊሲው ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን እና ከሚጠበቀው ከፍተኛ ግምት አንፃር፣ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና የተቀመጠለትን ዓላማ እንዴት እንደሚያሳካ መረዳት አስፈላጊ ነው። በዚህ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ በጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጂአይዜድ) አማካኝንት በኢትዮጵያ የተተገበረውን ሁሉን አቀፍ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና (TVET) ጥናት ውጤት አቅርበናል። በዚህ ፕሮግራም ስደተኞችን ተቀባይ ሀገር ነዋሪዎች እና ስደተኞች በጋራ ስልጠናውን የተከታተሉ ሲሆን፣ ዓላማውም ማኅበራዊ ትስስርን ማጎልበት እና የሥራ እድሎችን ማመቻቸት ነው። የጥናቱ ውጤቶቹ እንደሚያመለክቱት፣ በማኅበራዊ ትስስር በኩል የታዩ ተፅእኖዎች በብዙ ገፅታ ጥሩ ቢሆኑም፣ ከገቢ እና ከሥራ እድል አንጻር ውጤቶቹ ዝቅተኛ እና የተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ያተኮሩ ናቸው። አሃዛዊ እና አሃዛዊ ያልሆኑ (quantitative and qualitative) ማስረጃዎች የሚጠቁሙት ስልጠናው የማኅበራዊ ትስስርን ለማሳደግ እንደሚረዳ ነው፡፡ ከፕሮግራም ዲዛይን ወይም ከአፈጻጸም ችግሮች በላይ እንደ የሥራ እድሎች ውስንነት፣ የሕግ ማቆዎች እና የፆታ እኩልነትን መሰረት ያደረገ እድል ያለመኖር እና የመሳሰሉ በመዋቅራዊ ችግሮች ስልጠናው በስራ እድል ፈጠራ በኩል ውጤታማ እንዳይሆን ዋና መሰናክል ሆነው ይታያሉ። የጥናቱ ዋና ዋና ምክረ ሃሳቦች፥ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (ቴሙትስ) ሲታቀድ ጥንቃቄ በተሞላበት ጥናት ማለትም፤ ከጉልበት ገበያው አቅም እና ከህግ ማእቀፉ አንጻር በበቂ ሁኔታ መታየት አለበት፡፡ በተለይ የሥራ እድሎችን ከመፍጠር አንጻር ይህ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ማኅበራዊ ትስስርን ለማሻሻል ፤ አካታች የሆነ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ውጤታማ መሣሪያ ሆኖ ይስተዋላል። ነገር ግን ማኅበራዊ ትስስር ፣ ከሥራ እድል ፈጠራ እንደ ተጨማሪ ውጤት ብቻ ሳይሆን የስልጠናው ዋና ዓላማ ሆኖ የሚውሰድ ከሆነ፤ "ሌሎች የተሻሉ አማራጮች አልነበሩም ወይ?" የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በተለይ ከሥራ እድል ፈጠራ እና ከገቢ አንጻር በተያያዘ ባለን ማስረጃ መሰረት ጥያቄውን የበለጠ አስፈላጊ ያደርገዋል። አካታች የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና (ቴሙትስ) መርሃ ግብር የሚያመጣውን ለውጥ በተመለከተ፣ ሰፋ ያሉ ተጨማሪ ጥናቶችን ይፈልጋል። መሞላት ካለባቸው የእውቀት ክፍተቶች መካከል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና በስደተኞች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ፣ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ እና አወንታዊ ተጽዕኖ፤ ሊያስከትል የሚችለው ማኅበራዊ ተጽዕኖ፣ እንዲሁም በፆታ በኩል እና ከመካከለኛ እስከ የረዥም ጊዜ ያለው የሥራ እድል ፈጠራ እና ገቢ ላይ የሚኖሩት ውጤቶች ይገኙበታል።

Suggested Citation

  • Getachew, Abis & Höckel, Lisa Sofie & Kuhnt, Jana & Muhumad, Abdirahman A. & von Schiller, Armin, 2023. "ለስደተኞች እና ለስደተኛ ተቀባይ ማህበረሰቦች የስራ እድል እና ማህበራዊ ትስስርን ለማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና (Tvet) ያለው ሚና [Improving employment and social cohesion among refugee and host communities through TVET: evidence from an im," IDOS Policy Briefs 27/2023, German Institute of Development and Sustainability (IDOS), Bonn.
  • Handle: RePEc:zbw:idospb:283123
    DOI: 10.23661/ipb27.2023
    as

    Download full text from publisher

    File URL: https://www.econstor.eu/bitstream/10419/283123/1/PB-27.2023.pdf
    Download Restriction: no

    File URL: https://libkey.io/10.23661/ipb27.2023?utm_source=ideas
    LibKey link: if access is restricted and if your library uses this service, LibKey will redirect you to where you can use your library subscription to access this item
    ---><---

    Corrections

    All material on this site has been provided by the respective publishers and authors. You can help correct errors and omissions. When requesting a correction, please mention this item's handle: RePEc:zbw:idospb:283123. See general information about how to correct material in RePEc.

    If you have authored this item and are not yet registered with RePEc, we encourage you to do it here. This allows to link your profile to this item. It also allows you to accept potential citations to this item that we are uncertain about.

    We have no bibliographic references for this item. You can help adding them by using this form .

    If you know of missing items citing this one, you can help us creating those links by adding the relevant references in the same way as above, for each refering item. If you are a registered author of this item, you may also want to check the "citations" tab in your RePEc Author Service profile, as there may be some citations waiting for confirmation.

    For technical questions regarding this item, or to correct its authors, title, abstract, bibliographic or download information, contact: ZBW - Leibniz Information Centre for Economics (email available below). General contact details of provider: https://edirc.repec.org/data/ditubde.html .

    Please note that corrections may take a couple of weeks to filter through the various RePEc services.

    IDEAS is a RePEc service. RePEc uses bibliographic data supplied by the respective publishers.